ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተወሰደው የኃይል እርምጃ “ስህተት መሆኑን የኢትዮጰያ መንግሥት ባለሥልጣናት አምነዋል” ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ አስታውቀዋል፡፡ ግሪንፊልድ ለጋዜጠኞች ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ክልሉ ውስጥ የተፈጠረው ሁኔታ ምክንያቱ ሰፋ ያለ ስለመሆኑም የጋራ መግባባት እንዳለ ጠቁመዋል፡፡የቪኦኤን ዘገባ ያዳምጡ።

Read more

ፊት ለፊት ስራው፣ ከበስተጀርባ ደግሞ ህይወቱ ይገኛል፡፡ ሥራው የህይወቱ ማጣቀሻ ነው የሚሉ አሉ፡፡ በዚህም ሥራውን እንደ አነፍናፊ ውሻ አስቀድመው ህይወቱን ያንጎዳጉዳሉ፡፡ “እንዲህ ሲል የፃፈው በህይወቱ እንዲያ ስለሆነ ነው፡፡” በማለት ሥራና ህይወቱን ያጋባሉ፣ ያፋታሉ፡፡ ስለዚህ የደራሲ ቤት በሩ ቢዘጋም ከመግባትና ከመውጣት አይከላከልም፡፡ የደራሲ ደጃፍ ውሻ ቢታሰርበትም አያስፈራም፡፡ ቢታጠርም ከዘላዮች አያመልጥም፡፡ እኛ ዘንድ እንዲያ ለማድረግና ለመሆን የሚያስችል […]

Read more

በጋምቤላ ክልል በተቀሰቀሰ ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ ከሐሙስ ጥር 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ተባብሶ በቀጠለው ግጭት በክልሉ ውጥረት ነግሷል፡፡ ከጋምቤላ ክልል የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ በግለሰቦች መካከል የተነሳው አለመግባባት መልኩን ቀይሮ በኑዌርና በአኙዋ ብሔረሰቦች መካከል የከፋ ግጭት አስከትሏል፡፡ በዚህ ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች ሕይወት እንዳለፈና በርካቶች ለአካል ጉዳት እንደተዳረጉ የአይን እማኞች ለሪፖርተር […]

Read more

ዐፄ ቴዎድሮስ በበጌምድር ማንም ለሞተ ዘመዱ እንዳያለቅስ የሚል ዐዋጅ ዐውጀው ‹ሰው ሁሉ ዕንባውን ያጠጣ ነበር፡፡› በዚህ መካከል ደጃች ውቤ ሞቱና ለእቴጌ ጥሩወርቅ ወደ መቅደላ መርዶ ተላከ፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስም ሕዝቡን ‹ለደጃች ውቤ አልቅሱልኝ› ብለው አዘዙ። ሰውም ሁሉ ዘመዱ ሲሞት የቀረበት ልቅሶ ያን ጊዜ ወጣለት፡፡ ይህንን ያየች የበጌምድር አልቃሽ የኔታ ደጅ አዝማች ሁል ጊዜ ደግነት/ ዛሬ እንኳን […]

Read more

ኢትዮጵያውያን በወቅታዊ የአገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ሆነ በሌሎች ርእሶች ላይ በውጪም ሆነ በአገር ውስጥ መጽሐፍት ማሳተም ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል። በቅርቡ በአገር ውስጥ ከታተሙት መጽሐፍት አንዱ የዶክተር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ ታሪክ ፈተናዎችና የሚጋጩ ህልሞች የኢህአዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖለቲካ” የሚል መጽሐፍ ይገኝበታል። መጽሐፉ ሰለ ብሔራዊ መግባባት፥ ስለ ብሔራዊ እርቅ፣ ስለኢትዮጵያውያን የሚጋጩ ሕልሞችና ስለሌሎች ጉዳዮች በሰፈው ይተነትናል። […]

Read more

በሃዋሣ ከተማና በዙሪያዋ በሚገኙ ከተሞች ባለፈው እሁድ ጥር 5 የጀመረው የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለ5 ጊዜ መከሰቱን ተከትሎ ነዋሪዎችን ከፍተኛ ሥጋት ውስጥ ጥሏል፡፡ በሬክተር ስኬል 4.3 ይደርሳል የተባለው ይኸው ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት፤ በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ መደናገጥና ፍርሃትን የፈጠረ ሲሆን በተለይ የአዋሣ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ማስከተሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ርዕደ መሬቱ በዩኒቨርሲቲው አካባቢ በተደጋጋሚ መከሰቱን […]

Read more

በህወሓት አገዛዝ ቁጥጥር ስር የሚገኘው አየር ኃይል አብራሪ የነበረው አብዮት ማንጉዳይ ከ10 ዓመታት እስር በኋላ በረሃ ወርዶ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቀለ፡፡ 19.97 ዓ.ም የተደረገው ምርጫ ውጤት መጭበርበሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ አመፅ በኃይል ለመድፈቅ የህወሓት አገዛዝ አየር ኃይሉን ለመጠቀም በተጠንቀቅ እንዲቆም ማዘዙን በመቃወም ኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ይዞ ከአንድ ሌላ ጓደኛው ጋር ወደ ጅቡቲ የኮበለለው አብዮት ማንጉዳይ […]

Read more

በየዓመቱ የዲሞክራሲና ነፃነት አካሄድ በተመለከተ ጥናት የሚያካሄደው ፍሪደም ሃውስ፣ በዚህ ሳምንት የዓለም ነፃነት ሪፓርቱን ይፋ አድርጓል። ቡድኑ ዲሞክራሲን፤ የፖለቲካ ነፃንትንና የሰብአዊ መብት አያያዝን በሚመለከት ጥናት ያካሄዳል። የዚህ ዓመት ሪፖርቱ በ210 አገሮችና አካባቢዎች ውስጥ ያሉትን የፓለቲካ መብቶችና የህዝብ ነፃነቶችን አጥንቶና አመዛዝኖ በየዓመቱ በጥር ወር ይፋ የሚሆን ዘገባ ነው። ዓመታዊው ዘገባ በአለም ደረጃ ነፃነት የቀነሰበትን ምክንያት ጠቅሶ፣ […]

Read more

ዛሬ ከሰአት ከመሬት መንቀጥቀጥ ሽሸት ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ የነበሩ አምስት የሀዋሳ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መቂ ቆቃ አዋሽ ድልድይ ላይ ከአይሱዙ ኤፍ ኤስ አር ጋር የነበሩበት መኪና በመጋጨቱ ህይወታቸው በሚዘገንን ሁኔታ አልፏል፡፡ በትላንትናው እለት ባቀረብነው ዜና ዩኒቨርሲቲው በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ተማሪዎች መማርም መፈተንም ባለመቻላቸው ከታህሳስ 19 ቀን ጀምሮ መዘጋቱን የዩኒቨርሲቲው ሴኔት መወሰኑን መዘገባችን ይታወሳል። የዩኒቨርሲቲውን […]

Read more

በቅርቡ ለቻን የእግር ኳስ ውድድር ዘገባ ወደ ርዋንዳ የተጓዘው ጋዜጠኛ ወዳጃችን አወቀ አብርሀም በነበረበት ቡታሬ ከተማ የቴዲ አፍሮ “ላምባዲና” ሙዚቃ በጣም ተወዳጅ መሆኑን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስነብቦን ነበር፡፡ እኔም ከሰሞኑ የኬንያ ጉዞዬ የአወቀን መረጃ ትክክለኛነት ያረጋገጠልኝ አጋጣሚ ነበረኝ፡፡ ጃከስ ፉራሀ በርዋንዳ በኪጋሊ ዴይሊ የራደዮ ጣቢያ ነው የሚሰራው፡፡ ናይሮቢ ላይ ስንተዋወቅ ከኢትዮጵያ መሆኔን ሲያውቅ አስቀድሞ ያወራኝ […]

Read more