በኦሮሚያ ክልል የህዝብ ቁጣ ተባብሷል።ተቃውሞው በተለያዩ ቦታዎች እየተደረገ ነው።የመንግስት ወታደሮች መደብደብና በጥይት መግደላቸውን ቀጥለዋል።”ህዝቡ አትግደሉን፣ወታደሮች ከትምህርት ቤቶች ይውጡ፣ የገደሉት ለፍርድ ይቅረቡ፣የታሰሩት ይፈቱ”የሚል ጥያቄ እያቀረበ ነው።በድብደባና በጥይት አልበገር ያለው ህዝብ ላይ የመንግስት ወታደሮች ቦንብ እየወረወሩ ነው ይላሉ ነዋሪዎች።
ቪኦኤ በሆሮ ጉዱሩ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ የ1ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው የ7 ዓመቷ ሃና ገቢሳ ትምህርት ቤቷ በር ላይ በተወረወረ ቦንብ ስትቆስልና ስትወድቅ ወዲያውኑ አድማ በታኝ ፖሊስ ሌላውን ሰው መደብደቡን የአይን እማኝን ጠቅሶ ዘግቧል።የህፃኗ አጎት ሲገልጹ ” እውነት ነው የ7 ዓመቷ ሐና በቦንብ ተመታ ሆስፒታል ገብታለች። ጭንቅላቷ ሦስት ቦታ ላይ ቆስሏል። እናቷ ሃናን ስትወልድ በወሊድ ወቅት ባጋጠማት አደጋ ነው የሞተችው” ብለዋል።
በሆሮ ጉዱሩ ዞን አሊቦ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዱኛ ኡሬሶ የተባሉ መምህር በመንግስት ወታደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የአይን እማኝ የሆኑ መምህር ለቪኦኤ ገልጸዋል። “ተማሪዎቹ ወታደሮቹ ከግቢያችን ይውጡልን በመሳርያ ተከበን አንማርም፣የያዝነው ብህር ነው እንፈራለን ፣ልንማር እንጂ ልንደበደብ አልመጣንም በማለት ለወረዳው አስተዳደር ተናገሩ በዚህ ሰዓት ወታደሮቹ ተማሪውን መደብደብ ጀመሩ።የልጆቹ ጨኽት ያሳዘናቸው አንድ አርሶ አደር የትምህርት ቤቱን የሹቦ አጥር በጥሰው ልጆቹን አስመለጡ።ወታደሮቹ ግቢው ውስጥ ሌሎች ተማሪዎችን ሲፈልጉ አንድ መምህር ሴት ተማሪዎችን ጥበቃ ክፍል ውስጥ ሲደብቅ ይደርሱበታል ሲደበድበት ይወድቃል ከመሀከላቸው አንዱ ጨርሰው ሲል በጥይት ተኮሱበት”ብሏል።
ቪኦኤ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ዳግም የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ አመጽ የዘገበበትን ዘገባ ያዳምጡ።

አንድ መምሕር ተገድሏል፤ የሳባት ዓመት ታዳጊ ቆስላለች-VOA Amharic

| Uncategorized |
About The Author
-