ኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎችና ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ውስጥ ዛሬም ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭቶች እንደነበሩ ጉዳቶች መድረሣቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

“በመላው ኦሮሚያ መንግስት እየወሰደ ያለው ግድያና እስራት ህዝቡን ይበልጥ እንዳስቆጣውና በቀጣይ ከፍተኛ ቀውስ እንደሚፈጠር፤ ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ለቪኦኤ በሰጡት ቃለምልልስ ተናግረዋል።
ኦሮሚያ ውስጥ እየታየ ያለውን ሁኔታ ያነሣሣውና እያቀጣጠለ ያለው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የ24 አመት ግፍ ውጤት ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ወጣት በስርአቱ ተማሯል፣ድግሪ ይዞ ዲንጋይ ፈለጣ ውስጥ ነው የገባው። በዚህ ሰርዓት ላይ ተስፋ ቆርጧል። ዛሬ ሲጨንቃቸው ሞተዋል ያሏቸውን ድርጅቶች አሉ እያሉን ነው።ከወራት በፊት ግንቦት 7 እና ኦነግ ሞቷል በማለት በፓርላማው ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲናገር ነበር ዛሬ የህዝብ ብሶት ገንፍሎ ሲወጣ ከምን ጀርባ ግንቦት 7 አለ ኦነግ አለ በማለት ጭንቀታቸውን ደጋግመው ይናገራሉ ድርግ ትላንት እነሱኑ ይላቸው የነበረውን አንድ ችግር ሲነሳ “የውጪ ኃይሎች እጅ አለበት”ይላሉ ከአፄ ኃይለስላሴና ከደርግ የተማሩትን ደጋግመው ሲሉ ይሰማል።ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂቶች በልጽገው ብዙ ሰው በችግር ነው የሚኖረው ።ወጣቱ በአገሩ ተስፋ ቆርጦ በስደት ሊቢያ ላይ ታርደዋል፣ስንቱ እንደወጣ ቀርቷል በማለት ተናግረዋል። በሚፈጸመው ግድያ የተቆጡ በርካታ ወጣቶች ከሚሊሻ መሳሪያ እየቀሙ ጫካ እየገቡ ነው። በርዷል ህዝባዊ ቁጣው ማለት አይቻልም እያገረሸ ነው ያሉት ዶ/ር መራራ የርስ በርስ ግጭት እንዳይነሣ እንደሚሠጉ ገልጸው መቶ ሚሊዮን ህዝብን እያስፈራሩ እና እያሰሩ መግዛት አይቻልም ብለዋል።ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ሙሉውን ያዳምጡ።

ኢትዮጵያ “መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች” – ዶ/ር መረራ ጉዲና ቃለ ምልልስ-VOA Amharic

| Uncategorized |
About The Author
-